እዛም ቤት እሳት አለ

ቤተሰብ በአምላካችን በእግዚአብሔር በኤደን ገነት ውስጥ የተመሰረተ፥ የመጀመሪያው ተቋም ነው:: በመጽሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ ዘፍጥረት 1 (27-28) እንደተጻፈው እግዚአብሔር ቤተሰብን ሲያይ የሚያየው ባልና ሚስቱን፤ ከዛም ልጆቻቸውን፥ ብሎም ቀጣዩን ትውልዳቸውን ነው:: ስለዚህ ትውልድ የሚጀምረው ከቤተሰብ ነው ማለት ነው:: እንደ እግዚአብሔር ሃሳብ የተባረከ ትውልድ ለማፍራት የሚቻለው ደግሞ፥ ልጆች በአባትና በእናት ስር በፍቅርና በስነስርዓት ተኮትኩተውና ታንፀው ሲያድጉ ነው::

ነገር ግን ይሄ የእግዚአብሔር ተቋም(ቤተሰብ)፥ በተለይም ወላጅነት፥ ከፍተኛ ተግዳሮት እንደገጠመውና አሳዛኝና አስቸጋሪ ቦታ ላይ እንደሚገኝ ይታያል:: ለዚህም ምክንያቱ፥ ወላጆች እግዚአብሔር በቃሉ እንዳዘዘን ዘፍጥረት 18(19) ልጆቻችንን የእግዚአብሔርን መንገድ ይጠብቁ ዘንድ አላስተማርናቸውምና ነው:: ስለዚህ ይሄ ትውልድ በከፊል እግዚአብሔርን የማያውቅና የማይፈራ፥ ግብረገብነት የጎደለው፥ ወላጆችን የሚያሳዝንና የጥፋትን ጎዳና የተከተለ ሆኗል::

በተለይም ወደራሳችን ህብረተሰብ ስንመለከት፥ በአሜሪካን ሀገር የምንገኝ ወላጆች የሀገሩን ሰዎች የልጆች አያያዝ በደንብ ሳንረዳ፥ በሩቅ ባየነው እና በሰማነው ወሬ ተመስርተን አደራረጋቸውን ስለተከተልነው፥ ልጆቻችን ተገቢውን ስርዓት እንዲይዙ አላረግናቸውም:: የሀገሩን ሰው ማለትም የአሜሪካውያኑን የልጅ እንክብካቤ በጭፍን ለመከተል ያስደፈረን ምክንያት፥ የህዝቡ የስልጣኔ ደረጃና የሚኖሩበት በረከት፥ እንዲሁም አሜሪካ የዓለም ቁንጮ መሆኗ፥ ልጆቻችንን እነሱ እንደሚንከባከቡት ብንንከባከብ አሜሪካውያኑ የደረሱበት ደረጃ እንደርሳለን የሚል ግምት ኖሮን ሊሆን ይችላል::

ነገሩን ብናስተውለው ግን የደረሱበት ሥልጣኔና የሚኖሩበት በረከት፥ የአባቶቻቸው አምላክ እግዚአብሔር ከለቀቀላቸው ታላቅ ምህረት የተነሳ ነው ብዬ አምናለሁ:: ምክንያቱም የቀደሙት አባቶቻቸው ወደዚች ምድር የመጡት፥ በነፃነት ጌታን ለማምለክ ፈልገው ስለነበረ፤ ጌታ የሰጣቸውን ይችን ምድር፥ ራሳቸውንና ትውልዳቸውን አሳልፈው ለእግዚአብሔር የሰጡ፥ የእስራኤልን አምላክ በእውነት እና በመንፈስ የሚያመልኩ ነበሩ:: ዘጸአት 20(6) ወደ ዋናው ሃሳቤ ልመለስና በአሁኑ ጊዜ ያሉትን የምድሪቱን ሰዎች ተጠግተን ብናይ፥ እዛም ቤት እሳት አለ እንዲሉ በገጠማቸው በዚህ ዓመፀኛ ትውልድ የተነሳ ታውከዋል::

To Read The Full Articel Click here