እንደ እኛ የሆነ ሰው ነበረ

ያዕቆብ 5:17 ኤልያስ እንደ እኛ የሆነ ሰው ነበረ፥ ዝናብም እንዳይዘንብ አጥብቆ ጸለየ፥ በምድርም ላይ ሦስት ዓመት ከስድስት ወር አልዘነበም፤ ሁለተኛም ጸለየ፥18 ሰማዩም ዝናብን ሰጠ ምድሪቱም ፍሬዋን አበቀለች።

“እንደ እኛ የሆነ ሰው ነበረ” የተባለለት ኤልያስ ለመሆኑ ማን ነበረ?     ኤልያስ ከሰማይ እሳት ያወረደው?     ያ የሞተ ሰው ያስነሳው?  …ወደ ሰማይ በሰረገላ የሄደው? … ለእግዚአብሄር የቀናው?    ያዕቆብ ምነው ሌላ የሚመስለን ሰው ፈልገህ እንደእኛ ሰው ነበረ ወይም እሺ ፓውሎስም እንደ እኛ ሰው ነበረ ብትለን እኮ ይቀለን ነበረ። ምክንያቱም የብዙዎቻችን ህይወት በትንሹም ቢሆን ከፓውሎስ ጋር ይቀራረባል። እሺ ከብሉይ ኪዳንም ከሆነ የፈለከው “ዳዊትም እንደ እኛ ሰው ነበረ” ብትለን ጥሩ ነበር። ለምን ግን ኤልያስን መረጥክልን?።  ኤልያስን እኮ በዛ በተራራ ላይ ጌታ አንተ እና ጴጥሮስን ይዞ በወጣ ጊዜ የት እንዳለ አንተ እና ጴጥሮስ እኮ አይታችሁዋቸዋል። እሺ ጴጥሮስም እንደ እኛው የሆነ ሰው ነበረ ብትለን በደንብ ይገባኝ ነበር ምክንያቱም ያ ችኩሉ ጴጥሮስ ብዙ ጊዜ ሲሳሳት፣ ንስሐ ሲገባ ስለአየሁት ከእኔ ሕይወት ጋር ትንሽም ቢሆን ይቀራረባል። እንደውም ጥሩ ምሳሌ አገኘሁ… “ዘኪዎስም እንደ እኛው የሆነ ሰው ነበረ” ብትል ይመቸኝ ነበር።    ያ ዛፍ ላይ የወጣው… ጌታ ና ውረድ ብሎት ወደ ቤቱ የገባው… ያ ንሰሃ የገባው… ዘኪዎስ እኮ ለእኔ በቂ ነበር።   “ኤልያስ እንደ እኛ የሆነ ሰው ነበረ” ግን ትንሽ ከበደኝ… ይህቺን ቃል የሰጠኅን ለማጽናናት ነው ወይንስ በእርገጥ እንደ እኛ ሰው ነበር?  የምትለውን አምናለሁ ግን ያልገባኝ ነገር አለ …እኮ እኔም እኮ ብዙ ጊዜ እንደ ኤልያስ “ጌታ ሆይ እሳት አውርድ” ብዬ ጸልያለሁ። ታድያ የእኔ ጸሎት ለምን አልተመለሰም?

እሱ እኮ እከሌ ስለሆነ ነው፣ እሱ እና እኛን ማን አንድ አደረጋቸው?  እሱ እኮ ጻድቅ ነው፣ የሚለው ሃይማኖታዊ ምክንያተኛነት የመጽሐፍ ቅዱስን እውነታ ከሚጋርድብንና የተባልነውንና ናችሁ የተባልነውን እንዳንሆን ብዙ ጊዜ እንቅፋት ይሆንብናል።

የጌታ ወንድም የሆነው ያዕቆብ ስለ ጸሎት በጻፈበት በዚህ በአምስተኛው ምዕራፍ ላይ ጽሑፉን “ኤልያስ እንደ እኛ የሆነ ሰው ነበረ”። በማለት በማጽናኛ ያጠቃልልናል። ያዕቆብ ይህቺን ጥቅስ የምዕራፍ አንድ መጀመርያ ቢያደርጋት ብዙ ክርስትያኖች በተለይም የዘመኑ ጥቅስ መዛዦች የያዕቆብን መጽሐፍ ተመራጭ የንባብ መጽሐፋቸው ያደርጉት እንደነበር አልጠራጠርም። ዛሬ ብዙ የስህተት አስተማሪዎች ኢየሱስም በምድር ሲመላለስ “እንደ እኛው ሰው ነበረ” ለማለት በሚዳፈሩበት ዘመን እስቲ በደረጃችን ዝቅ ብለን እንደ እኛው ሰው ነበሩ የተባሉትን እያየን እራሳችንን እንመርምር።

እሱ እኮ እከሌ ስለሆነ ነው፣ እሱ እና እኛን ማን አንድ አደረጋቸው?  እሱ እኮ ጻድቅ ነው፣ የሚለው ሃይማኖታዊ ምክንያተኛነት የመጽሐፍ ቅዱስን እውነታ ከሚጋርድብንና የተባልነውንና ናችሁ የተባልነውን እንዳንሆን ብዙ ጊዜ እንቅፋት ይሆንብናል። “እንደ እኛ የሆነ  ሰው ነበረ” የተባለለት ኤልያስ ለመሆኑ ማን ነበረ?

ያዕቆብ 5 16: የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች። 17 ኤልያስ እንደ እኛ የሆነ ሰው ነበረ፥ ዝናብም እንዳይዘንብ አጥብቆ ጸለየ፥ በምድርም ላይ ሦስት ዓመት ከስድስት ወር አልዘነበም፤ ሁለተኛም ጸለየ፥18 ሰማዩም ዝናብን ሰጠ ምድሪቱም ፍሬዋን አበቀለች።

”ከስድስት ቀንም በኋላ ኢየሱስ ጴጥሮስንና ያዕቆብን ወንድሙንም ዮሐንስን ይዞ ወደ ረጅም ተራራ ብቻቸውን አወጣቸው። 2 በፊታቸውም ተለወጠ፥ ፊቱም እንደ ፀሐይ በራ፥ ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ። 3 እነሆም፥ ሙሴና ኤልያስ ከእርሱ ጋር ሲነጋገሩ ታዩአቸው።“