አብዛኛዎቹ አገልጋዮች ተቀባይ እንጅ ሰጪ አይደሉም። የብዙዎቹ ወዳጅነት የሚመሰረተው ከምዕመናን በሚቀበሉት ስጦታ ነው። ከቤተ ክርስትያን አስራት ጀምሮ ፓስተርየ አሳሰበኝ እያለ የሚሸጉጠውን ማለቴ ነው።
አገልጋዮች ቀለብ አያስፈልጋቸውም ወይም በሚያገለግሉት ምዕመናን ሊባረኩ አይገባም አይደለም ሃሳቤ ከምዕመናኑ ጋር የምንመሰርተው ወዳጅነት ግን በጥቅም ላይ የተመሰረተ ሊሆን አይገባውም ነው። ።።።።።።………።።።።።።።።።።።።።።።……………
ከአባቱ ጋር ያወዳጀን ልጁ ጌታ ኢየሱስ አሁንም ለሚኖረን ህብረት ወይም ወዳጅነት ማዕከል እርሱ መሆን አለበት። ይህን ጌታ በጥቅም ልንለውጠው አይገባም። በተለይ የወዳጅነት ማዕከላቸው ጥቅም አድርገው የሚንቀሳቀሱ እረኞች ምዕመኑን የመገሰጽ ወይም የጌታን ቃል በድፍረት የማስተማር አቅም የላቸውም። ውሻ በበላበት ይጮሃል አይደል ተረቱ። ላበላቸው ነው የሚጮኹት…ለጌታ ሳይሆን ለወዳጃቸው….ከዚህም አልፈው ቃሉን ያመቻምቻሉ….እረ ምን ይህ ብቻ ምዕመኑ በረጠባቸው ገንዘብ ተባረኩ ይላሉ….ታዲያ በድፍረትና በኩራት የማይሞኩሯትን የመባረኪያ መንገድ ያስተምራሉ….እነርሱ መቀበልን እንጂ መስጠትን አያውቁም። ታዲያ የሚያስተምሩትን ትምህርት ሳይኖሩበት ባለጠጋዎች ናቸው።..
በዘመናችን ታላላቅ ወንጀል የሚሰሩት በሃይማኖት ስም ወይም በፈጣሪ ስም ነው። በቅርብ የሳውዲ ንጉስ ቤተሰቦች 2 ቶን አደንዛዥ እጽ በግል አውሮፕላን ይዘው ሊበሩ ሲሉ የቤሩት መንግስት በቁጥጥር ስር አድርጓቸዋል። ይህ ብቻ አይደለም ውስኪ ስሽጥላቸው የነበረው ሰው የሰራውን ዶክመንታሪ በCNN ቴሌቪዥን መገረም ተመልክተናል፣ ሲያስፈልጋቸውም ለገብኝት ወደ ቬጋስ ጎራ እያሉ የግልሙትና ርሃባቸውን እንደሚያስታግሱ ለዓለም የተገለጠ ነው። ነገር ግን ሳውዲ ይህን ሲፈጽም ተገኘ እየተባለ እጅና አንገት የሚቆረጥባት አገር ነች።
ሽብርተኛው ISIS የሰው አንገት በአሰቃቂ ሁኔታ የሚያርደው አምላክ ብሎ በሚጠራው አላህ ስም አይደለምን? ታዲያ የዘመናችን ቁጭ በሉዎች ለጌታ ብለው በስጡ ስብከት የምስኪኑን ኪስ የሚያርዱ መንፈሳዊ ካባ ያጠለቁ ተናጣቂ ተኩላዎች አይደሉምን።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ልቡን ምድሩ ላይ የቸከለ በላይ ያለውን ማሰብ የተሳነው አለዛም በየዋህነት በአብርሃም በረከት ሊንበሸበሽ ያለችውን ያራግፋል። ባዶ ማድጋህ ዘይት ይሞላል ይሉታል……ባዶ ሽሮ አሮበት….እህል እየናፈቀው የሽንብራ መግዣውን ያርዱበታል።…………………………እነርሱ እያበሩና እየደለቡ ምዕመኑ እየገረጣ …እየከሳ ብሎም በጌታ ላይ እያኲረፈ ከጌታ ቤት ይቀራል።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ኑሮ ዳገት የሆነበትና ከወር እስከወር መድረስ ተስኖት በእዳ የሚኳትነውን ምስኪን አስራትህን ባትከፍል ሌባ ነህ ይሉታል። ቃሉን የማያውቅ ምስኪን ነገር ግን ፈሪሃ እግዚአብሔር ያለው ወንድም እየተጨነቀ እንደተሻረው ኪዳን ደስታ የራቀው አገልግሎት ይፈጽማል።
ልብ በሉ የአንዳንዶቹ ደሞዝ ከምእመኑ አንዱ እንኳን ያን ያህል አይከፈለውም፣ ነገር ግን የእርሱ እንዳይጎድል ሌሎችን ያስጨንቃል…በእግዚአብሔር ቃል እያጣቀሰ ያስፈራራል። ………………………….መድረክ ላይ በፋሽን ሱፍ በአጌጠ ከራባት ሁሌ በአዳዲስ ልብስ ሁልግዜ የሚገለጡት ያለምንም ሃፍረት ሰርተው እንዳገኙት አድርገው የጌታ ባርኮት ይሉናል።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ያ እውነተኛ አገልጋይ ይህ አይነቱን አገልግሎት ነበር የተጸየፈው። ድንኳን እየሰፋ ምድሪቱን በወንጌል ያረሰው። ………………………………ዛሬ የቤተ ክርስትያን መከፋፈል ዋናው ምክንያት የገንዘብ ፍቅር ነው። ይህ የክፋት ስር የተባለው የገንዘብ ፍቅር እርስ በእርስ ያናክሳል፤ይከፋፍላል። ምዕመናን ምክንያቱን ሳያውቁት በቲፎዞ ከጀርባ በመሰለፍ አብሮ ይናከሳል።
አገልግሎት በጌታ ጸጋ መሆኑ ቀርቶ ራሱ በችሎታው እንዳደረገው በመቁጠር “ይገባዋል” የሚሉ አጨብጫዎች ለራሱ ይሰበስባል።…….
ዛሬ የእነዚህ የሆድ አገልጋዮች ግማት በዓለም ዘንድ ወጥቶአል። ከታላላቅ ሚድያዎች BBC፣ CNN ጅምሮ እስከ ሃገራችን መጽሄቶች ትኩስ ዜና ሆኖአል።የጌታ ስም ከመቸውም ግዜ እየተሰደበ ያለው በእነዚህ የሆድ አገልጋዮች ነው።
።።።።።።።።።።።።።።።።፡።።።።።።።።።።።።።።።።
እናንተ የሆድ አገልጋዬች ከጌታ ተማሩ። በምድረ በዳ ጌታ ሲያስተምር የዋለውን ህዝብ “በሉ አሁን ለአገልጋዬች የሚሆን የፍቅር ስጦታ ሰብስቡልን” አላለም….እውነተኛው እረኛ ይልቁንስ ለመንጋው በመራራት ወደ ደቀ መዛሙርቱ ዞር ብሎ “እንመግባቸው ዘንድ ምግብ የት ይገኛል” አለ እንጂ…እና በቅባቱ ታምራት ሰርቶ ርሃብተኛውን መገበ እንጂ አልነገደበትም…ይህ ብችም አይደለም ይህ እውነተኛ እረኛ ህይወቱን ስለ በጎቹ ሰጠ። ዛሬ ነፍሳችሁን አትጠየቁም ፣ ግድየለም ተውት ቢያንስ እስኪ ከራሱ ከህዝቡ ሰብስባችሁ በከበራችሁበት ገንዘብ ለራበው ለጠማው ለተቸገረው ማካፈልን በተግባር አስተምሩ። እስከ መቸ ምንደኛ ትሆናላችሁ? ።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
በዘመናችን በገንዘብ ተደራድረው የሚያገለግሉ አገልጋዬች የበዙበት፣ ያም ባይሆን የሚሰጣቸውን ዳርጎት በማሰብ የሚውተረተሩ “አደረ ለሆዱ” የሆኑ አገልጋዮች እጅግ ብዙ ናቸው። የገንዘብ ፍቅር ብቻ ሳይሆን ክብርን የተጠሙ በየቤተ ክርስትያን መሰብሰብያ ሆነ አደባባይ ፓስተርዬ ፓስተርዬ መባልን የሚውዱ፣ ሁሉን ለማስጎንበስ የሚዳዱ የዘመናችን ፈሪሳውያኖች የበዙበት ዘመን ነው።
ቃሉን እንደ ልባቸው ፈቃድ የሚተረጉሙ፣ መንፈስ ቅዱስ የራቃቸው የመድረክ ተዋኞች ናቸው። ነጣቂ ተኩላዎች የተባሉ አንዳች ነገር ለማግኘት በጥቅስ ብዛት ህዝቡን የሚዘበዝቡ ውሃ አልባ ደመናዎች ናቸው።
መንፈሳዊና ስጋዊ ርሃብ ለጎዳው ህዝብ ደንታ የሌላቸው የማይጨበጥ ተስፋ የሚያዘግኑ በሰው ችግር የሚቀልዱ ዘባቾች ናቸው።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ከእንደዚህ አይነት ነጣቂዎች እንዴት እንጠበቅ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
1ኛ ተስፋችን ጌታ ክርስቶስ ብቻ እንደሆነና ሃገራችን በሰማይ እንደሆነ እናስብ ” እኛ አገራችን በሰማይ ነውና፥ ከዚያም ደግሞ የሚመጣ መድኃኒትን እርሱንም ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን እንጠባበቃለን፤”
(ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 3:20)
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
2ኛ ገንዘባችን ስንሰጥ የትኛውም ስጦታ በደስታ ሊሆን ይገባዋል።ጌታ ማንንም አያስገድድም። ” እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጠውን ይወዳልና እያንዳንዱ በልቡ እንዳሰበ ይስጥ፥ በኀዘን ወይም በግድ አይደለም።”
(2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 9:7)
።።።።።።።።።።.።.።።።.።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
3ኛ ለጌታ የምንሰጠው በትክክል ለጌታ ስራ መዋሉን እናረጋግጥ። “እናንተ መስጠት ብቻ ነው የሚጠበቅባችሁ ሌላው አያገባችሁም” የሚሉንን አይሆንም ማለት አለብን።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
4ኛ ለቤተ ክርስትያን ይሁን ለሚንስትሪ ስንሰጥ ሃላፊነት ወስዶ የተረከበ ሰው ቢያንስ በ6ወር አንድ ግዜ ግልጽ የሆነ የሂሳብ ሪፓርት ሊያቀርብ ይገባዋል። እንዲሁም ከመሪዎች ዉጭ በሆነ ሰው ሂሳቡ ኦዲት ተደርጎ ቢያንስ በአመት አንድ ግዜ በገንዘቡ ለሚደግፈው ህዝብ መቅረብ አለበት።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
5ኛ ከሁሉ በላይ ስንሰጥም ሆነ ማንኛውንም ነገር ስናደርግ የማይሳሳተውን ጌታ በመጠየቅ ከስሜታዊነት እና ከግብዝነት በጸዳ መንፈስ እናድርግ።
።።።።።።።።።።።።።.።።።.።።።።።።።።።።።።።።።።።.
ስብሃት ለእግዚአብሔር ።